ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን...

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከምእመናን እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው፦ "ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መመሪያ መካከል ለመተኛት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ ልክ ዱዐ እንደሚያረግ ሰው መዳፋቸውን ሰብስበው ከፍ ያደርጉት ነበር። በሱም ላይ ከትንሽ ምራቅ ጋር በመቀላቀል ቀለል ያለ መንፋት በአፋቸው እየነፉበት ሶስት ምእራፎች ያነቡበታል። {ሱረቱል ኢኽላስ}ን፣ {ሰረቱል ፈለቅ}ን፣ {ሱረቱ አንናስ}ን ከዚያም የቻሉትን ያህል የሰውነታቸውን ክፍል ከጭንቅላታቸው፣ ከፊታቸውና ከሰውነታቸው የፊትለፊት ክፍል በመጀመር በመዳፋቸው ያብሱታል። ይህንንም ድርጊት ሦስት ጊዜ ይደጋግሙታል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከመተኛት በፊት የኢኽላስን ምእራፍና ሙዐወዘተይንን መቅራትና ምራቅ የቀላቀለን ትንፋሽ በመንፋት የተቻለውን ያህል የሰውነትን ክፍል ማበስ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል