ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።"
ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ከሶላት አራቁቶ እንደመቃብር የማይሰገድበት ማድረግን ከለከሉ። በመቀጠልም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ ከሚቀራበት ቤት እንደሚሸሽ ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቤት ውስጥ ሱና ሶላቶችን የመሰሉ አምልኮዎችን ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. ወደ ሺርክና በተቀባሪው ላይ ወሰን ወደ ማለፍ ከሚያዳርሱ መንገዶች አንዱ ስለሆነ ከጀናዛ ሶላት በስተቀር መቃብር ግቢ ውስጥ ሶላት መስገድ አይፈቀድም።
  3. መቃብር ዘንድ መስገድ መከልከሉ ሶሐቦች ዘንድ የተረጋገጠ ጉዳይ ስለሆነ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ልክ እንደመቃብር የማይሰገድባቸው ከማደረግ ከለከሉ።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል