በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከአቢ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምሽት ውስጥ የበቀራህ ምእራፍ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው አላህ መጥፎና ጎጂ ከሆኑ ነገሮች እንደሚበቃው ተናገሩ። ለሌሊት ሶላት ከመቆም ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ሌሎች ውዳሴዎችን ከማለት ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ለሌሊት ሶላት የሚቀራ ዝቅተኛው በቂ የቁርአን አንቀፆች ናቸውም ተብሏል። ከዚህም ውጪ ተብሏል። ምንአልባት ሁሉም ከላይ የተጠቀሱትን ትርጓሜዎችን ቃሉ ስለሚሰበስባቸው ሁሉም ትክክለኛ ትርጓሜ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሱረቱል በቀራህ የመጨረሻ አንቀፆች ትሩፋት መገለፁ። እሱም { አመነ አርረሱሉ …} ከሚለው የአላህ ንግግር እስከምእራፉ መጨረሻ ያለውን ነው።
  2. የበቀራህ ምእራፍ መጨረሻዎች ምሽት ላይ ለሚቀራቸው ሰው ከጉዳት፣ ከመጥፎና ከሰይጣን ይከላከላሉ።
  3. ምሽት ፀሃይ በመግባት ጀምሮ ጎህ በመውጣቱ ይጠናቀቃል።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል