ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።...

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰው ቁርአንን በልቡ ከሸመደደው በኋላ እንዳይረሳው ቁርአንን በመጠባበቅና በማንበቡ ላይ መዘውተርን አዘዙ። ቁርአን ከልብ ውስጥ ከታሰረች ግመል የበለጠ እጅግ የሚጠፋና የሚወገድ መሆኑን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመሀላቸው በማጠናከር ገለፁ። ግመል በክንዶቿ መሀል በገመድ ተጠፍራ ስታበቃ ሰውዬው ከተጠባበቃት ይይዛታል፤ ከለቀቃት ግን ትሄዳለችም ትጠፋለችም።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቁርአንን የሸመደደ ሰውም ቁርአንን በማንበቡ ላይ በየጊዜው ከዘወተረ ልቡ ውስጥ እንደተጠበቀ ይቀራል። ያለበለዚያ ግን ይጠፋበታልም ይረሳዋልም።
  2. ቁርአንን ከመጠባበቅ ጥቅሞች መካከል ምንዳና አጅርን ማግኘትና የትንሳኤ ቀን ከፍተኛ ደረጃን መጎናፀፍ ነው።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል