ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከዑስማን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።"
ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች መካከል በላጩና አላህ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ቁርአን ማንበብን፣ መሸምደድን፣ ማሳመርን፣ መገንዘብንና ማብራራትን የተማረና እርሱ ዘንድ ያለውን የቁርአን እውቀት ከመተግበሩም ጋር ለሌላው ያስተማረ መሆኑን ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የቁርአን ልቅና መገለፁ። ቁርአን የአላህ ቃል ስለሆነ ምርጡ ቃል ነው።
  2. ምርጥ ተማሪ ማለት ሌላውንም የሚያስተምር እንጂ በነፍሱ ላይ የሚገደብ አይደለም።
  3. ቁርአንን መማርና ማስተማሩ ማንበቡንም፣ ትርጉሙንም ህግጋቱንም ያካትታል።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል