አይሁዶች ቁጣ የሰፈነባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ ናቸው።

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከዓዲይ ቢን ሓቲም እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "አይሁዶች ቁጣ የሰፈነባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይሁዶች እውነትን እያወቁ ባለመተግበራቸው አላህ የተቆጣባቸው ህዝቦች እንደሆኑ ተናገሩ። ክርስቲያኖች ደግሞ ያለ ዕውቀት የሚሰሩ ስለሆኑ የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዕውቀትና ተግባርን ሰብስቦ መሄድ ቁጣ ከሰፈነባቸውም ከተሳሳቱትም ሰዎች መንገድ መዳኛ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ከአይሁዶችና ክርስቲያኖች መንገድ መጠንቀቅና ቀጥተኛ የሆነውን የኢስላምን ጎዳና አጥብቀን መያዝ እንዳለብን እንረዳለን።
  3. በመሰረቱ አይሁዶችም ክርስቲያኖችም የተሳሳቱና ቁጣ የሰፈነባቸው ህዝቦች ናቸው። ነገር ግን ልዩ መገለጫቸው የአይሁዶቹ ቁጣ የሰፈነባቸው መሆናቸው ሲሆን የክርስቲያኖች ልዩ መገለጫ ደግሞ መሳሳታቸው ነው።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል