ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር...

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
አቢ ዐብዲረሕማን አስሱለሚይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ፦ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር። በዚህም "ዕውቀትንም ተግባርንም ተማርን" አሉ።" ብሎ ነገረን።
ሐሰን ነው። - አሕመድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ሰሐቦች -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ይቀስሙ ነበር። በቀሰሙት አስር አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀት እስኪረዱና እሱን ሳይተገብሩ ወደ ሌላ እውቀት አይሸጋገሩም ነበር።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ደረጃና ቁርኣንን የመማር ጉጉታቸውን፤
  2. ቁርኣንን መማር የሚባለው በመረዳትና ውስጡ ባለው በመተግበር ነው እንጂ በማንበቡና በመሸምደዱ ብቻ አይደለም።
  3. ዕውቀት ከንግግርና ከተግባር በፊት እንደሆነ ተረድተናል።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል