{ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብሏል፦ " {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።"
ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

የተከበረው ቁርኣን ምዕራፎች በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ ሲወርዱ የሚጠናቀቁበትና ከሌላው ምእራፍ የሚለዩበትን መንገድ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አያውቁም ነበር። ይህ ግን {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነበር። እሷ ከወረደች በኋላ ያለፈው ምእራፍ እንደተጠናቀቀችና {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} ለአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ እንደሆነች አወቁ በማለት ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ገለፁ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. "ቢስሚላሂ" ከሱረቱል አንፋልና ተውባህ በስተቀር በምዕራፎች መካከል መለያ ነው።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል