ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።

Scan the qr code to link to this page

ሓዲሥ
ትንታኔ
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች
ምድቦች
ተጨማሪ
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። - Al-Bukhari as Mu‘allaq/hanging, with a decisive form

ትንታኔ

የአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ እጅግ ጉጉ እንደነበሩና በሁሉም ወቅት፣ ስፍራና ሁኔታ ላይ ሆነውም አላህን ያወሱ እንደነበር ተናገረች።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህን ለማውሳት ከትንሹም ሆነ ከትልቁ ሐደሥ መፅዳት መስፈርት አይደለም።
  2. ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ ዘውታሪ እንደነበሩ እንረዳለን።
  3. መፀዳዳትን በመሰለ አላህን ማውሳት በሚከለከልባቸው ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከመከተል አኳያ በሁሉም ሁኔታ ላይ አላህን ማውሳት በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ምድቦች

በተሳካ ሁኔታ ተልኳል